በአዲስ አበባ የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና በይፋ ተጀመረ

AMN- ሰኔ 8/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች የአንደኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና መውሰድ ጀምረዋል።

የዘንድሮውን ከተማ አቀፍ ፈተና የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር)፣ በዳግማዊ ሚኒልክ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት በይፋ አስጀምረዋል።

የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናውን 85 ሺህ 17 ተማሪዎች ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

667 ትምህርት ቤቶች በ199 ፈተና ጣቢያዎች ተማሪዎቻቸውን እያስፈተኑ ነው።

የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻልና የላቀ ስኬት ለማስመዝገብም ሰፊ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውንም የቢሮ ኃላፊው ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

ከተደረገው ዝግጅት አኳያም ዘንድሮ ካለፉት ዓመታት የተሻለና አበረታች ውጤት እንደሚጠበቅ ኃላፊው ገልጸዋል።

በፍቃዱ መለሰ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review