AMN – ሰኔ 08/2018

ቮዚንሃ የስፔኑን ብሄራዊ ቡድን ተጫዋች ላሚን ያማልን በ21 ዓመት እና በ40 ቀናት ይበልጠዋል።
ይህ በእግር ኳስ ውስጥ አልፎ አልፎ የሚታይ ድንቅ ክስተት ሲሆን፣ የ40 ዓመቱ ግብ ጠባቂ በዚሁ እድሜው ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለም ዋንጫ ተሳትፎ አድርጓል።

ላሚን ያማልም በ18 ዓመት እና በ334 ቀናት እድሜው በዓለም ዋንጫ በመሳተፍ ተመሳሳይ ታሪክ አለው።
ሆኖም፣ የኬፕ ቨርዴው ግብ ጠባቂ ከስፔን ጋር ባደረጉት ጨዋታ ላይ እያሳየዉ ብቃት እጅግ አስገራሚ ነው።
በፖርቹጋል ሁለተኛ ሊግ የሚጫወተው ቮዚንሃ፣ ተጫዋቾች ወደ እሱ የሚመጡትን ኳሶች የሚቆጣጠርበት መንገድ፣ የእግር ኳስ ማህበረሰቡ እንደ አንድ ክለብ የጋራ አድናቆት እንዲቸረው አድርጎታል።

በ40 ዓመቱ በሰማይ ላይ እንደ ንስር እየበረረ እና በእርጋታ የሚጫወተዉ ቮዚንሃ ለኬፕ ቨርዴ የሚችለውን ሁሉ አበርክቷል።

ኬፕ ቨርዴ ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለም ዋንጫ ከመሳተፏም በላይ ከስፔን ጋር በዚህ መልኩ መፎካከሯ አድናቆትን እያተረፈ ሲሆን፣ በተለይም የ40 ዓመቱ ጎልማሳዉ ግብ ጠባቂ እያሳየ ያለው ብቃት ከአድናቂዎች እጥፍ ድርብ ምስጋና እንዲቸረው አድርጎታል።

በጨዋታዉ ኬፕ ቨርዴ ስፔንን ነጥብ በማስጣል ታሪክ የሠራች ሲሆን ጨዋታዉ 0 ለ 0 በሆነ ውጤት ተጠናቋል።
የኬፕ ቨርዴውን ግብ ጠባቂ ብቃት በአንድ ቃል እንዴት ትገልጹታላችሁ? ሀሳባችሁን አካፍሉን!
በወንድማገኝ አሰፋ