የንግድ ምክር ቤቱ የሀገራዊ ምክክር ሂደቱ ስኬታማ እንዲሆን የድርሻውን ይወጣል

AMN – ሰኔ 10/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከኢትዮጵያ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጋር በሀገራዊ የምክክር ሂደት “የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ ምን መሆን አለበት” በሚሉ ጉዳዮች ላይ ወይይት እያካሄደ ይገኛል።

በውይይቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ንግድና ማህበራት ዘርፍ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት አይናለም አባይነህ( ዶ/ር) ምክር ቤቱ የግሉን ዘርፍ በመወከል በሀገራዊ ጉዳዮች ከመንግስት ጋር በመነጋገር ለተሻለ ሀገራዊ እድገት የበኩሉን ድርሻ ይወጣል ሲሉ ተናግረዋል ።

በሀገራዊ ምክክር ሂደቱ ለግሉ ዘርፍ ሰላምን ከማምጣት በሻገር ለኢኮኖሚው መፍትሄን የሚያመጣ እንደሆነም አክለዋል ።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባዬ ኦገቶ (ዶ/ር) በበኩላቸው የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በ1ሺ 234 በሚደርሱ ወረዳዎች ላይ የአጀንዳዎች ልየታ እና የአጀንዳ ማሰባሰብ ስራን መስራቱን ተናግረዋል።

በፌደራል ደረጃ 38 ተቋማት እና ማህበራት ውይይት አድርገው አጀንዳቸውን ለኮሚሽኑ መስጠታቸውን የገለፁት ኮሚሽነር አምባዬ፣ ዛሬ በተለይ የግል ዘርፉን የወከለው የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከዚህ ቀደም ለኮሚሽኑ አጀንዳውን ማቅረቡ ወሳኝ እርምጃ መሆኑን ተናግረዋል።

በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው የሚመጡ ውጤቶች ተግባራዊ እንዲሆኑ የግሉ ዘርፍ ተዋንያን የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡም ተጠይቋል፡፡

በወንድማገኝ አበበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review