AMN ሰኔ 14/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ውጤት ማሳወቂያ መርሐ-ግብር አካሄዷል፡፡
ቦርዱ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ የምርጫ ክልል በተካሄደዉ የ7ኛዉ ጠቅላላ ምርጫ የድምጽ አሰጣጥ ሂደት አብላጫ መቀመጫ ያገኙትን ተወዳዳሪዎች ይፋ አድርጓል፡፡
በአዲስ አበባ በሚገኙ 10 የምርጫ ክልሎች ለክልል ምክር ቤት ከቀረቡ 158 መቀመጫዎች መካከል ብልጽግና ፓርቲ 134 መቀመጫዎችን ሲያገኝ ኢዜማ 8 መቀመጫዎችን ማግኘቱን ቦርዱ ይፋ አድርጓል፡፡
ቦርዱ ይፋ ባደረገዉ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ውጤት መሰረት ፡-
የአዲስ አበባ የምርጫ ክልል ብዛት – 10
አጠቃላይ የክልል ምክር ቤቱ መቀመጫ ብዛት – 158
ብልጽግና ፓርቲ – 134 መቀመጫዎች
ኢዜማ ፓርቲ – 8 መቀመጫዎች
አንድ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ – 4 መቀመጫዎች
ህዳሴ ፓርቲ – 2 መቀመጫዎች
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር – 2 መቀመጫዎች
ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት – 2 መቀመጫዎች
ሰላም ለኢትዮጵያ ጥምረት – 2 መቀመጫዎች
የወላይታ ህዝቦች የነፃነት ንቅናቄ – 1 መቀመጫ
የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ – 1 መቀመጫ
የወሎ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ – 1 መቀመጫ
አቶ ዳንኤል ጌታቸዉ ጋረደዉ የግል ተወዳዳሪ – 1 መቀመጫ ማግኘታቸዉን ቦርዱ ይፋ አድርጓል፡፡
በአዲስ አበባ በተካሄደዉ 7ኛዉ ጠቅላላ ምርጫ 1 ሚሊዮን 957 ሺህ 676 መራጮች ድምጽ ለመስጠት የተመዘገቡ ሲሆን ከነዚህ መካከል 96 መቶ የሚሆኑት መራጮች በየምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ድምጽ ሰጥተዋል፡፡
በወንድማገኝ አሰፋ