ኬፕ ቨርድ ከኡራጓይ ጋር አቻ በመለያየት ሌላ ነጥብ አሳካች

AMN-ሰኔ 15/2018 ዓ.ም

ኬፕ ቨርድ ከኡራጓይ ጋር 2ለ2 በመለያየት ሌላ ነጥብ ማሳካት ችላለች።

ለአፍሪካዊቷ ሀገር ኬቨን ፒና እና ሄሊዮ ቫሬላ ሁለቱን ግቦች አስቆጥረዋል።

ለኡራጓይ ማክሲሚሊያኖ አራሆ እና አጉስቲን ካኖቢዮ ሁለቱን ግቦች አስመዝግበዋል።

ኬፕ ቨርድ በመጀመሪያ ጨዋታ የ2010 የዓለም ዋንጫ አሸናፊ ስፔንን ፤ አሁን ደግሞ የሁለት ጊዜ የዓለም ዋንጫ አሸናፊዋ ኡራጓይ ጋር ተፋልማ ሁለት ነጥብ አግኝታለች።

በዓለም ዋንጫ የተሳተፈች ሦስተኛ ትንሽ ሀገር ኬፕ ቨርድ የመጀመሪያ የዓለም ዋንጫዋን የበለጠ ደማቅ ለማድረግ በመጨረሻ የምድብ ጨዋታዋ ሳውዲ አረቢያን ትገጥማለች።

በተመሳሳይ ሁለት ነጥብ ያላት ኡራጓይ ምድቡን ከምትመራው ስፔን ጋር ትጫወታለች።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review