የህዝብ ድምጽ አሸንፏል፤ ኢትዮጵያ በልጆቿ ጸንታለች!

መላው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ዴሞክራሲን በማፅናታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን ደስ አለን!

የተከበራችሁ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ለፓርቲያችን ብልፅግና የሰጣችሁት ድምፅ የቃል ኪዳናችን ማሰሪያ በማድረግ የጣላችሁብን አደራ በላቀ ስኬት ለመመለስ እንተጋለን።

ይህ ምርጫ ኢትዮጵያ ያሸነፈችበት የሀገራችን የዴሞክራሲ ጉዞ ወደ አዲስ ምዕራፍ የተሻገረበት ደማቅ የታሪካችን አካል ሆኖ ተመዝግቧል ።

በመዲናችን አዲስ አበባ በተደረገው የከተማ ምክር ቤት ምርጫ፣ ፓርቲያችን ብልፅግና ከጠቅላላው 158 መቀመጫዎች ውስጥ 134፤ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከ23ቱ የምክር ቤት መቀመጫዎች ውስጥ 20 መቀመጫዎችን በማግኘት የህዝብን ሙሉ አመኔታና አብላጫ ድምፅ በማግኘት አሸንፏል።

በሌላ በኩል ከ158 የከተማ ምክርቤት መቀመጫዎች ውስጥ 11 የተፎካካሪ ፓለቲካ ፒርቲዎች 23 የግል ተወዳዳሪ 1 ወንበሮች ያገኙ ሲሆን አዲስ አበባ ከምትወከልበት ከ23ቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎች ውስጥ

የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች 2 እንዲሁም የግል ተወዳዳሪ 1 ወንበሮችን ማሸነፍ ችለዋል።

ይህ እጅግ አስደናቂ ዉጤት እያደገ የመጣዉን የሰለጠነ የፖለቲካ ባህል እና የህዝብን ፍትሐዊ ዳኝነት ያሳያል። በጥቅሉ ፓርቲያችን በአብላጫ ድምፅ ቢያሸንፍም በዋናነት ያሸነፈዉ መላው የመዲናችን ነዋሪ ፣ ሰላም እንዲሁም ልማት እና እያደገ የመጣዉ የዴሞክራሲ ባህል ነው።

የተከበራችሁ መራጮቻችን ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከለሊት እስከ ለ‍ሊት በምርጫ ጣቢያዎች በመሰለፍ ምርጫው ነጻ፣ ፍትሃዊ፣ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ አግባብ እንዲጠናቀቅና ለብልፅግና ፓርቲ አብላጫ ድምፅ በመስጠት እምነት ለጣላችሁብን ለቀጣዩ ጉዟችንም የህዝብ አደራን በአግባቡ እንድንወጣ አቅማችን ለሆናችሁ በሙሉ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

በቀጣዩ የ5 ዓመቱ ጉዟችን ህዝባችን የሰጠንን ታላቅ አደራ በገባነው ቃል መሠረት ሌት ተቀን በመሥራት፣ የከተማችንን ብሎም የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግናን እውን ለማድረግ ተግባራዊ ምላሽ እንሰጣለን።

በተለመደው መልኩ ከህዝባችን ጋር በመተባበር በከተማችን የተጀመረውን የለውጥ ጉዞን በማሳለጥ የህዝባችን ኑሮ እና አኗኗር ለመለወጥ ያለንን ቁርጠኝነት ዳግም እናረጋግጣለን!

ይህ ድል የብልፅግና ፓርቲ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ ድል ነው!

ዲሞክራሲን እያፀናን ልዩነቶቻችንን በሰለጠነ መንገድ እያስተናገድን፣ በአንድነትና በፓርቲያችን መሪነት ወደ ላቀ ከፍታ እንጓዛለን።

ምርጫውን በማስፈጸም፣ በመታዘብ ፣ ሰላምን በማስጠበቅ ዉጤታማ ስራ የሰራችሁ እንዲሁም የኢትዮጵያን እውነት ለዓለም በማሳየት ረገድ የሀገሪቱን ህግና ስርዓት ተከትላችሁ የዘገባችሁ የሚዲያ ተቋማት ከሁሉ በላይ የሀገራችሁ ዴሞክራሲ አንድ እርምጃ ወደፊት እንዲራመድ የበኩላችሁን የተወጣችሁ በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ!

በመጨረሻ በሀገር አቀፍም ሆነ በከተማ ደረጃ የፖለቲካ ልዩነት ወደ ፖሊሲ አማራጭ በማሳደግ በዚህ ምርጫ ላይ ተፎካክራችሁ በህዝብ ይሁንታ ወንበር በማግኘት የአዲስ አበባ ምክርቤት አባል ለመሆን የበቃችሁ የ11 ፖለቲካ ፓርቲዎች ወኪሎችና አንድ የግል ተወዳዳሪ በሰላማዊ መንገድ ህዝባችሁን ለማገልገል ዕድል በማግኘታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንወዳለን ።

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና በልጽጋ ለዘላለም ትኑር! እንኳን ደስ አላችሁ

የብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review