AMN- ሰኔ 22/2018 ዓ.ም
ማንኛውም ተቋም የተጣለበትን የሕዝብ ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት እንዲችል በሳይንሳዊ ዘዴ የተደገፈ የጥናትና ምርምር ሥራ ወሳኝ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ቡዜና አልከድር ገለጹ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የጥናትና ምርምር ሥራዎችን መገምገሚያ ውይይት መድረክ አካሄዷል።
በዚሁ ወቅት የአዲስ አበባ ከተማ ምከር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ቡዜና አልከድር፣ ማንኛውም ተቋም የተጣለበትን የሕዝብ ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት እንዲችል በሳይንሳዊ ዘዴ የተደገፈ የጥናትና ምርምር ሥራ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

ከጥናት እና ምርምር ሥራዎች የተገኙ ግኝቶችን እና ምክረ ሀሳቦችን ተግባራዊ ለማድረግ የዛሬው ውይይት አጋዥ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
በሕግ ማውጣት ተግባር፣ የክትትል፣ ቁጥጥርና ድጋፍ ሥራዎች፣ የህዝብ ውክልና እና ተሳትፎ፣ ዝርዝር የተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ፣ የ3ኛው ዙር ምክር ቤት ጠቅላላ ስኬት ጥናት የተደረገባቸው ዘርፎች ናቸው።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አዲስ ምዕራፍ፣ የአዲስ አበባ የማዘጋጃ ቤት አገልግሎቶች እና የአዲስ አበባ ከተማ የአስተዳደርና ትራንስፎርሜሽን የሁለት ስትራቴጂክ እቅድ ዘመኖች ንጽጽራዊ ጥናት ላይ ያተኮረ የጥናትና ምርምር ሥራዎች ላይ ውይይት ተካሄዷል።
በዳንኤል መላኩ