በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

You are currently viewing በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

AMN – ሰኔ 29/2018 ዓ.ም

በ2018 የትምህርት ዘመን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተሰጠው የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የማለፊያ ነጥብ ይፋ ተደረገ።

ለአጠቃላይ ተማሪዎች ማለፊያ ነጥቡ 50 በመቶና ከዚያ በላይ እንዲሆን ተወስኗል።

ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች 45 በመቶ እንዲሆን የተወሰነ ሲሆን፣ ለኦቲዝም፣ ለዳውን ሲንድረም እና ለአእምሮ ዕድገት ውስንነት ላለባቸው ተማሪዎች ደግሞ የማለፊያ ነጥቡ 40 በመቶ እንዲሆን ተደርጓል።

የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) ፣ የዘንድሮውን የተማሪዎች ውጤት ለማሻሻል ሰፊ ስትራቴጂካዊ ሥራዎች መከናወናቸውን ጠቁመዋል።

በተለይም መደበኛውን የክፍል ትምህርት ለማገዝ የተሰጠው የማጠናከሪያ ትምህርት እንዲሁም ተማሪዎች በሂሳብና በእንግሊዘኛ ትምህርቶች ላይ የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ተቀርጾ የተተገበረው ልዩ ዕቅድ ለዚህ ስኬት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከቱን ገልጸዋል።

ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) ለውጤቱ መገኘት ባለድርሻ አካላትን አስተባብረው ለሠሩ የትምህርት ማህበረሰብ አባላት በሙሉ ምስጋና አቅርበዋል።

በተለይም ፈተናውን በአጭር ጊዜ አርመው ውጤቱ ፈጣን በሆነ መልኩ ይፋ እንዲሆን ቀን ከሌሊት የደከሙ የፈተና ክፍል ባለሙያዎችንና ሂደቱን በቅርበት ሲደግፉ የነበሩ የሥራ መሪዎችን አመስግነዋል።

የቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሳምሶን መለሰ በበኩላቸው፤ በ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን 84 ሺህ 737 ተማሪዎች በ199 የፈተና ጣቢያዎች ፈተናውን መውሰዳቸውን ገልጸው፣ የዘንድሮው አጠቃላይ ውጤት ካለፉት ዓመታት አንጻር አበረታች ዕድገት ማሳየቱን መግለፃቸውን ከከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review