AMN ሐምሌ 6/2018 ዓ.ም
የኢኮኖሚ መረጋጋት እና የኑሮ ውድነትን ማቃለል፡- የከተማዋ ነዋሪ ቀዳሚ ጥያቄ የሆነውን የኑሮ ውድነት መቋቋም ዋነኛ የትኩረት ሥራ ይሆናል።
የሥራ ዕድል ፈጠራ፡- የኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ የሚመጡ ዕድሎችን በመጠቀም በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የሥራ አጥነት ምጣኔን መቀነስ።
የመሠረተ-ልማት አስተዳደር፡- ባለፉት ዓመታት የተገነቡ ግዙፍ መሠረተ-ልማቶችን እና የኮሪደር ልማቶችን መጠበቅና አገልግሎታቸውን በዘላቂነት ማስቀጠል።
የሀብት አያያዝና ጥገና ፡- አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ከመጀመር ጎን ለጎን የተገነቡ መንገዶችን፣ መናፈሻዎችንና መብራቶችን በጥራት የመያዝና የመጠገን ባህል ላይ በጀት መመደብ።
የከተማ ውበትና ፅዳት፡- የተገነቡ የኮሪደር መስመሮች ጽዱ እና አረንጓዴ ሆነው እንዲቀጥሉ ከህብረተሰቡና ከግሉ ዘርፍ ጋር የተቀናጀ አሰራር መዘርጋት።
ትራንስፖርት እና የትራፊክ ፍሰት፡- ከከተማዋ ፈጣን እድገት ጋር አብሮ የሚሄድ ቀልጣፋ የሕዝብ ትራንስፖርት አቅርቦትና አስተዳደር ሥርዓትን ማጠናከር።

መልካም አስተዳደርና ዲጂታላይዜሽን፡- ብልሹ አሰራርን ለመቀነስ በ”አዲስ መሶብ” 50 በመቶ የደረሰውን አገልግሎት ወደ 100 በመቶ በማሳደግ አሰራሩን ሙሉ በሙሉ ማዘመን።
የማህበራዊ ልማት ማጠናከር፡- የተማሪዎች ምገባና አልባሳት አቅርቦትን ማስቀጠል፤ እንዲሁም አዲስ አበባን የጤና ቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ የጤና ባለሙያዎችን አቅም ማሳደግ።
የገቢ አሰባሰብና ፋይናንስ ዲሲፕሊን፡- ለዘላቂ ልማት የሚውሉ ገቢዎችን በአግባቡ መሰብሰብ፣ የታክስ መሠረቱን ማስፋት እና ቁጠባን ማረጋገጥ።
ሰላምና ጸጥታን ማረጋገጥ፡- የማኅበረሰብ አቀፍ የጸጥታ አደረጃጀቶችን በማጠናከር ወንጀልን መቀነስ፣ እንዲሁም ሕገ-ወጥ የመሬት ወረራና ግንባታን በመከላከል የሕግ የበላይነትን ማስፈን።
የቤት ልማት ፕሮግራሞች፡- የነዋሪውን የቤት ጥያቄ ለመመለስ በመንግስት፣ በግል ዘርፍና በሕብረት ሥራ ማኅበራት የቤት ልማትን በስፋት ማከናወን።
የውሃ እና የመንገድ ፕሮጀክቶች፡- የተጀመሩ ሜጋ የውሃ አቅርቦት ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ፣ እንዲሁም የመንገድ መሰረተ ልማትን በማስፋፋት ኔትወርኩን ማጠናከር።
በአጠቃላይ አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ ስሟና ግብሯ የተናበበ ስማርት ከተማ ለማድረግ የጀመርነው ልማት በጥራት፣ በስፋትና በፍጥነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታውቀዋል።