በጉለሌ ክፍለ ከተማ በአንድ ጀንበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሐ ግብር በደማቅ ሁኔታ በመከናወን ላይ ይገኛል

You are currently viewing በጉለሌ ክፍለ ከተማ በአንድ ጀንበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሐ ግብር በደማቅ ሁኔታ በመከናወን ላይ ይገኛል

AMN – ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም

ኢትዮጵያ በየዓመቱ አዲስ የስኬት ታሪክ እያስመዘገበችበት ያለውና በታላቅ የህዝብ ንቅናቄ የሚከወነው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር፤ ዛሬ በአንድ ጀንበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ በጉለሌ ክፍለ ከተማ በተለያዩ ቦታዎች የበርካታ ህዝብ ተሳትፎ በታከለበት ተጀምሯል።

በችግኝ ተከላ መርሐግብሩ ላይ የተሳተፉት ነዋሪዎች እንደገለጹት፤ ዛሬ ኢትዮጵያውያን ተስፋን እየተከልን የዕድገትና የብልጽግና ጉዟችንን በጋራ ማሳየት የምንችልበት አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ነው ብለዋል።

በዚህ ታላቅ ዕለት ሚሊዮኖች በአንድነት ወጥተው ችግኞችን በመትከል ለአንድ ሀገራዊ ዓላማ የቆሙና ለነገዋ ሀገር አርቆ አሳቢዎች መሆናቸውን የሚያሳይ ተግባር መሆኑንም ተሳታፊዎቹ ገልጸዋል።

በተጨማሪም በጋራ በመሆን ችግኞችን መትከል የኢትዮጵያውያንን የቆዩ የጋራ የመልማት ባህላዊ እሴቶች ዳግም ሕያው እንዲሆኑ የሚያስችል ከመሆኑም በላይ፣ በአንድ ሀገራዊ ዓላማ ዙሪያ የሚተጉ ህዝቦች መሆናቸውን በተግባር የሚያረጋግጥበት የህብረ-ብሔራዊነት አንዱ ማሳያ መሆኑን አስረድተዋል።

ከማለዳው 12:00 ሰዓት ጀምሮ በርካታ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚደረገው የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ላይ በንቃት በመሳተፍ አረንጓዴ አሻራቸውን እያሳረፉ ይገኛሉ።

በወርቅነህ ንጋቱ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review