የአጀንዳ የሥራ ቡድኖች የምክክር ሂደቱን በይፋ ጀምረዋል

AMN- ሐምሌ 30/2018 ዓ.ም

በስልታዊ ቡድኖች ተደራጀተው የቀረቡ የምክክር ምክረ-ሃሳቦች 500 አባላት ላሉት ለአጀንዳ የሥራ ቡድን መቅረባቸውን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ገልጿል፡፡

መድረኩ በእያንዳንዱ የአጀንዳ የሥራ ቡድን ሁለት የተደራጁ የቃለ-ጉባኤ ሃሳቦች የተነበቡ ሲሆን የሁለቱ ቡድኖች ሃሳቦች በአጀንዳ ተቀራራቢነት፣ ተመጋጋቢነት እና ልዩነት በተመካካሪዎች እንዲታይ እድል ሰጥቷል፡፡

ተመካካሪዎች ከሁለቱ ስልታዊ ቡድኖች ሃሳቦችን እንዲያቀናጁ 30 አባላት ያሉበትን የምክረ-ሃሳብ አቀናጆችን መርጠዋል፡፡

በቀጣዮቹ ቀናት የስልታዊ ቡድኖች ሃሳቦች በተመረጡ አቀናጆች ተዋህደው እንደሚቀርቡ የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review