AMN- ነሐሴ 15/2018 ዓ.ም

ካቢኔው በዛሬው ስብሰባው በቀረቡ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አስተላልፏል፡፡
በዚህ መሠረት፦

1- የማህበረሰብ ጤና አቀፍ መድህን ተጠቃሚዎች መዋጮን ለማሻሻል የቀረበ የውሳኔ ሀሳብ ተወያይቶ ተግባራዊ እንዲሆን አፅድቋል።

2- ሀገራዊ ፋይዳ ላላቸው ፕሮጀክቶች (ለሆቴል፣ ለሞልና አፓርትመንት፣ ኢንዱስትሪ፣ ለበጎ አድራጎት፣ መንግስታዊ ተቋማት እና የህክምና ተቋማት) የማስፋፍያና አዳዲስ የመሬት ጥያቄዎች ለመመለስ የቀረበ የውሳኔ ሀሳብ ላይ ተወያይቶ ተፈፃሚ እንዲሆን አፅድቋል።

3- በከፊል በኮሪደር ለምተው፣ በከፊል ሳይለሙ የቆዩ አካባቦዎችን በተሟላ ሁኔታ ለማልማት የቀረበ የውሳኔ ሀሳብ ላይ ተወያይቶ ተግባራዊ እንዲሆን ማጽደቁን ከአዲስ አበባ ከንቲባ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።