ሀገራዊ የምክክር ሂደት ለሀገሪቱ ዘላቂ ሰላምና ብልጽግና መሠረት የሚጥል ታሪካዊ አጋጣሚ ነው – ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ

You are currently viewing ሀገራዊ የምክክር ሂደት ለሀገሪቱ ዘላቂ ሰላምና ብልጽግና መሠረት የሚጥል ታሪካዊ አጋጣሚ ነው – ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ

AMN – ነሐሴ 16/2018 ዓ.ም

የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዚዳንትና የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ በኢትዮጵያ የተካሄደው ሀገራዊ የምክክር ሂደት ለሀገሪቱ ዘላቂ ሰላምና ብልጽግና መሠረት የሚጥል ታሪካዊ አጋጣሚ መሆኑን ገለጹ።

ኦባሳንጆ በምክክር ጉባኤው የማጠቃለያ ስነ ስርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር ፣ አራት ዓመታት የፈጀ ዝግጅት የተደረገበትና 4ሺህ ተሳታፊዎችን በማሳተፍ ለ46 ቀናት ሲካሄድ የቆየው ይህ ሀገራዊ ምክክር መጠናቀቁ ትልቅ ታሪካዊ ስኬት መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ሂደት ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም ቢሆን በተሞክሮነት የሚወሰድ አርአያነት ያለው ተግባር መሆኑን ጠቁመዋል።

ከቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር በመሆን በአፍሪካ ህብረት ስም የተሰጣቸውን የሰላም ኃላፊነት መሠረት በማድረግ ለኢትዮጵያ ሰላም፣ ደህንነትና መረጋጋት እስከ መጨረሻው አብረው እንደሚቆሙ አረጋግጠዋል።

ኦባሳንጆ ለኢትዮጵያ መንግሥትና ለሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ላስመዘገቡት ስኬት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈው፣ የተጀመረው የሰላም መንገድ ወደ ታላቅ የጋራ ብልጽግና እንደሚያሸጋግር እምነታቸውን ገልጸዋል።

በታደሰ ሽፈራው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review