በመዲናዋ ለሥራ ፈላጊዎች የሚሰጠው ሥልጠና ክህሎት መር የሥራ ስምሪት እንዲኖር አስችሏል

You are currently viewing በመዲናዋ ለሥራ ፈላጊዎች የሚሰጠው ሥልጠና ክህሎት መር የሥራ ስምሪት እንዲኖር አስችሏል

AMN- ነሐሴ 25/2018 ዓ.ም

በመዲናዋ ለሥራ ፈላጊዎች የሚሰጠው ሥልጠና ክህሎት መር የሥራ ስምሪት እንዲኖር ማስቻሉን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ የሥራ እና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ሚሊዮን ማቲዮስ ገለጹ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2019 በጀት ዓመት እና በቀጣይ 5 ዓመታት እቅዶች ላይ ውይይት አካሂዷል፡፡

በዚህም ባለፉት አምስት ዓመታት ብቻ ከ2 ሚሊየን በላይ ነዋሪዎች በተለያዩ ዘርፎች የሥራ እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ የሥራ እና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ሚሊዮን ማቲዮስ፤ በከተማዋ አዳዲስ ስልጠና የሚሰጥባቸው ኮሌጆች እንዳሉ አንስተዋል፡፡

በእነዚህ ኮሌጆች ለሥራ ፈላጊዎች የሚሰጠው ሥልጠና ክህሎት መር የሥራ ስምሪት እንዲኖር አስችሏል ብለዋል፡፡

በዚህም የዜጎችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ተችሏል ያሉት አቶ ሚሊዮን ማቲዮስ፤ በመዲናዋ የሥራ እድል ፈጠራን ማሳደግ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በመዲናዋ በቀጣዮቹ 5 ዓመታት ውስጥ ለ2 ነጥብ 5 ሚሊየን የከተማዋ ነዋሪዎች አዲስ የሥራ እድል ለመፍጠር መታቀዱን ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

ይሄንን ተግባራዊ ለማድረግም ክህሎት መር የሥራ ስምሪት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል፡፡

ኮሌጆችም የሚሰጧቸውን ስልጠናዎች ጥራታቸውን በጠበቀ መልኩ ማስቀጠል እንዳለባቸውም ጠቁመዋል፡፡

ለዚህ ውጤታማነትም ሥልጠና የሚሰጡ ተቋማትን የማዘመን እና የማደራጀት፣ የብድር አቅርቦት እንዲሁም የመስሪያ ቦታ የማዘጋጀት ተግባራት እየተከናወኑ ስለመሆኑ ገልጸዋል፡፡

የሻምበል ምህረት

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review