
AMN- መስከረም 03/2019 ዓ.ም
የብሪክስ ጉባኤ ሁለተኛው ቀን ላይ ከካዛኪስታን ፕሬዚዳንት ቃሲም ጆማርት ቶካዬቭ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለፁ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት በዲጂታላይዜሽን፣ በንግድና ኢንቨስትመንት እንዲሁም በመከላከያ መስኮች የትብብር ዕድሎችን ለማስፋት እና በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን አጋርነት ይበልጥ ማሳደግ በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ መክረናል ብለዋል፡፡