የመስቀል ደመራ በዓል በመስቀል አደባባይ በተለያዩ ሀይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች እየተከበረ ነው

You are currently viewing የመስቀል ደመራ በዓል በመስቀል አደባባይ በተለያዩ ሀይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች እየተከበረ ነው
default

AMN መስከረም 16/2019

የመስቀል ደመራ በዓል በመስቀል አደባባይ በተለያዩ ሀይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች እየተከበረ ይገኛል።

በሥነ ሥርዓቱ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ባስልዮስ ማርቶማ ማቴዎስ ሣልሳዊ፣ የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ፣ ብፁዓን አባቶች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች፣ ዲፕሎማቶች ታድመዋል።

በተጨማሪም የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን፣ የእምነቱ ተከታዮች እና ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ጎብኚዎችም በበዓሉ ተገኝተዋል።

የደመራ በዓል ሃይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች እየተከናወኑ ሲሆን በዓሉን የተመለከቱ ያሬዳዊ ዝማሬዎችም በመቅረብ ላይ ናቸው።

የመስቀል ደመራ በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በየዓመቱ ከሚከበሩ ሃይማኖታዊ በዓላት መካከል አንዱ ነው።

በዓሉ እ.አ.አ በ2013 በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የዓለም ቅርስ ሆኖ መመዝገቡ ይታወሳል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review