AMN – መስከረም 28/2019 ዓ.ም

በአፍሪካ አህጉር በግንባር ቀደምትነት ከተቋቋሙት ዘመናዊ የአቪዬሽን ተቋማት አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ አየር ኃይል በአፍሪካ ከሚገኙ ጠንካራና አይበገሬ የአየር ኃይሎች መካከል ቀዳሚዉ ነዉ፡፡

አየር ኃይሉ ላለፉት ዘጠኝ አስርት አመታት የኢትዮጵያን የአየር ክልል በጽናት ከመጠበቁም በላይ የተሰጡትን ግዳጆች በሙሉ በብቃት የፈጸም አቅም መገንባቱን በይፋ አስመስክሯል፡፡
ተልዕኮዉን በላቀ ደረጃ መፈጸም እንዲያስችለዉ ባለብዙ ተልዕኮ ተዋጊ ጄቶችን የጦር ሂሊኮፕተሮችን እና አዳዲስ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ታጥቋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር ኃይል በራስ አቅም በሚያዘምናቸው ሄሊኮፕተሮች፣ በዘመናዊ ተዋጊ ጀቶቹ እና በቴክኖሎጂ ምጥቀቱ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ክብር ከፍ ያደረገ ኩራት ነው።
በዘመናዊ የጦር ቴክኖሎጂዎች ብቻ ሳይሆን በጽኑ ሃገራዊ ፍቅር፤ በታላቅ ህዝባዊ ወገንተኝነት እና በላቀ ጀግንነት የተገነባ መሆኑ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚያስጠብቅ አስተማማኝና አይበገሬ ተቋም ለመሆን በቅቷል፡፡
በትውልድ ቅብብሎሽ፤ በጠንካራ ሙያዊ ሥነ ምግባር እና ቴክኖሎጂ የተገነባዉ ተቋሙ የበርካታ የአፍሪካ ሀገራትን የአየር ኃይል አባላት በማሠልጠን የአህጉሪቱ የዕውቀት ማዕከል ሆኗል፡፡
ንስሮቹ ያለፉበት ፈታኝ ውጣ ውረድ የሀገርን ሉዓላዊነት ከማስከበር ባለፈ፣ የሌሎች ሀገራትን የአየር ክልል የመጠበቅና የመከላከል ብቃታቸዉን ለማረጋገጥ ችለዋል፡፡
በወንድማገኝ አሰፋ