AMN- ጥቅምት 2/2019 ዓ.ም

የሰንደቅ ዓላማ ቀን እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ለሃገሩ ያለውን ፍቅር ክብር እና ቃልኪዳን በልቡ የሚያድስበት ነው ሲሉ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀ ስላሴ ገለጹ፡፡
19ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሠንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን” በሚል መሪ ሐሳብ እየተከበረ ነው፡፡
በአከባበሩ ላይ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀ ስላሴ ባደረጉት ንግግር፤ ለ19ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ አላማ ቀን እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል፡፡
የሰንደቅ ዓላማ ቀን እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ለሀገሩ ያለውን ፍቅር ክብር እና ቃልኪዳን በልቡ የሚያድስበት ነው ብለዋል፡፡
እንዲሁም ህብረ ብሔራዊ ኢትዮጵዊ ማንነትን በጋራ የምናጎለብትበት ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ሰንደቅ አላማ የብሄራዊ ህብረት ማሳያ እና የዜጎች ሃገራዊ ፍቅር እንዲሁም ብሄራዊ ስሜት መገለጫ የስነ-ልቦና አንድነት ማጽኛ ምልክት መሆኑንም አንስተዋል፡፡
እንዲሁም የመስዋዕትነት፣ የነጻነት የሉአላዊነት እና የግዛት አንድነት መለኪያ፣ የህዝቦች እኩልነት እና የህብረታችን ህያው ምስክር ጭምር ነው ብለዋል፡፡
በሥነ ሥርዓቱ ላይ የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች አባላት፣ ለምክር ቤቱ ተጠሪ የሆኑ ተቋማት፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
የሻምበል ምህረት