AMN ግንቦት 18/2018 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የላፍቶ ሆስፒታል መመረቁን አስመልክቶ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት የላፍቶ ሆስፒታል የህክምና አገልግሎት አሰጣጥን ከመቀየር ባለፈ፣ ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፎች እራሷን ለመቻልና ለሀገራዊ ልማት ያላትን ጽኑ ቁርጠኝነት የሚያሳይ ህያው ምስክር ነው ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ በተሻሻለው የመከላከል እና አክሞ የማዳን የጤና ፖሊሲ መሠርት ፣ ሀገራችንን ቀዳሚ የህክምና ቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ፣ ለህክምና ወደ ውጭ ሀገር የሚወጣውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ለመቀነስ ለሰነቅነው ርዕይ እና መሰል የረቀቁ የዘርፉ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ግንባታን ለማስቀጠል የላፍቶ ሆስፒታል አሻጋሪ ምዕራፍ ነው ብለዋል።
በ5.4 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ዘመናዊና ግዙፉ የላፍቶ ሆስፒታል እጅግ ዘመናዊ አቅሞች በመጠቀም እንደ ካንሰር፣ ውስብስብ የልብ ህመም እና ተያያዥ የህክምና ሁኔታዎችን ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ህክምና የሚሰጥ ሲሆን፣ ዜጎች እዚሁ ሀገራቸው ውስጥ ልዩ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላል።

ይህ ታላቅ ተቋም የህክምና አገልግሎት አሰጣጥን ከመቀየር ባለፈ፣ ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፎች እራሷን ለመቻልና ለሀገራዊ ልማት ያላትን ጽኑ ቁርጠኝነት የሚያሳይ ህያው ምስክር ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡