ጠላት የሚፈራው ወዳጅ የሚመካበት የኢትዮጵያ ብርቱ ክንድ

You are currently viewing ጠላት የሚፈራው ወዳጅ የሚመካበት የኢትዮጵያ ብርቱ ክንድ

AMN- ጥቅምት 21/2019 ዓ.ም

የምሥራቅ አፍሪካ የኃይል ማዕከል እና የሉዓላዊነት ተምሳሌት የሆነችው ኢትዮጵያ፣ የውስጥና የውጭ ጫናዎችን ተቋቁማ ሰላሟንና ልማቷን ለማስቀጠል የሚያስችላትን የመከላከያ አቅሟን የማዘመን ሥራ ወደ ላቀ ምዕራፍ አሸጋግራለች።

የሀገሪቱን ጸጥታና ደኅንነት በአስተማማኝ ዐለት ላይ ለማነጽ ትኩረት የሰጠው መንግሥት፤ በቅርቡ በሩሲያ-አፍሪካ ጉባዔ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተረከቧቸውን 12 የሱ-35 አራተኛ ትውልድ የጦር ጄቶች ጨምሮ በርካታ ዘመናዊ መሣሪያዎችን በማስታጠቅ አቅሙን የላቀ ደረጃ ላይ እያደረሰው ይገኛል።

ይህ እርምጃ ኢትዮጵያን ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ቀዳሚ እንደሚያደርጋትና እስከ 2030 እ.ኤ.አ. ወደ አምስተኛ ትውልድ የጦር መሣሪያ አቅም ለመሸጋገር የተያዘውን ስትራቴጂካዊ እቅድ ከግብ ለማድረስ ትልቅ መሠረት የሚጥል ነው።

ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጨምሮ ግዙፍ መሠረተ ልማቶችን ለመጠበቅ የሚያስችል ዘመናዊ አቅም የተገነባ ሲሆን፤ ሠራዊቱ በአየርና ምድር ጦር አቅም የበላይነት እየተቀዳጀ ይገኛል።

በተጨማሪም የውጭ ሀገራት ጥገኝነትን ለማስቀረት የተቋቋመው ስካይ ዊንግ ኤሮናቲክስ ኢንዱስትሪ የጦርና የሲቪል ድሮኖችን በሀገር ውስጥ በማምረት፣ በመገጣጠምና በመጠገን የቴክኖሎጂ ነፃነት እያረጋገጠ ይገኛል።

ከጥንት ከጋሻና ጦር አንስቶ እስካሁን የዘለቀው የኢትዮጵያ ውትድርና ታሪክ አሁን ላይ በኮምፒዩተራይዝድ አሰራር፣ በድሮን ቴክኖሎጂ እና በከፍተኛ ሳይንሳዊ እውቀት የተገነባ ኃይል ሆኗል።

ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ከሰው ኃይል ጋር ማቀናጀት ውጊያን በርቀት ለመቆጣጠር፣ ረጅም ጊዜ የሚወስዱ ጦርነቶችን በአጭር ለመቋጨት የሚያችል አቅም የገነባችው ኢትዮጵያ ፣ ብርቱ ክንዷ ለወዳጆቿ መመኪያ ሆናለች።

የዓለም ሀገራት የሚፈራ ሠራዊት በመገንባታቸው ሙሉ ትኩረታቸውን በልማት ላይ ማድረግ እንደቻሉ ሁሉ፣ ኢትዮጵያም ጠንካራ መከላከያ መገንባቷ ለሀገራዊ ሜጋ ፕሮጀክቶች መሳካት ዋስትና ሆኗታል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ደሙን አፍስሶ የሀገርን ዳር ድንበር በመጠበቁ እና ማንኛውንም የሚቃጣ ጥቃት የሚያመክን ዝግጁነት ያለው መሆኑ ሀገሪቱ ሙሉ ትኩረቷን በልማት ሥራዎች ላይ እንድታደርግ ያስችላታል፡፡

#ትልቅሃገር#ትልቅህዝብ#ታላቅርዕይ#አዲስአበባ#ኢትዮጵያ

#አዲስሚዲያኔትዎርክ#የትዉልድድምጽ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review