የኢትዮጵያ ሚዲያ ልህቀት ማዕከል ክፍተትን መሰረት ያደረገ ስልጠና ለመስጠት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ተገለጸ

You are currently viewing የኢትዮጵያ ሚዲያ ልህቀት ማዕከል ክፍተትን መሰረት ያደረገ ስልጠና ለመስጠት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ተገለጸ

AMN- ጥቅምት 26/2019 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ሚዲያ ልህቀት ማዕከል ክፍተትን መሰረት ያደረገ ስልጠና ለመስጠት እና ሙያዊ ስነ ምግባር ያከበረ ባለሙያ ለማፍራት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ገለጸ።

የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል እና የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ቦርድ ሰብሳቢ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴንን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ የመገናኛ ብዙሃን ባለቤቶች፣ አመራሮች እና የዘርፉ ምሁራን በተገኙበት የኢትዮጵያ ሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመርቋል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሐይማኖት ዘለቀ፤ የኢትዮጵያ ሚዲያ ልህቀት ማዕከል ክፍተትን መሰረት ያደረገ ስልጠና ለመስጠት እና ሙያዊ ስነ ምግባር ያከበረ ባለሙያ ለማፍራት ከፍተኛ አበርክቶ አለው ብለዋል፡፡

በተለይም እንደ ሀገር ያለውን የዘርፍ ጋዜጠኝነት ባለሙያ ክፍተት ለመሙላት የልህቀት ማዕከሉ ድርሻው የላቀ እንደሚሆን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ሚዲያ ልህቀት ማዕከል ዘመናዊ ቴክኖሎጂን አሟልቶ ዘመኑ የሚጠይቀውን ስልጠና ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ለመስጠት የሚያስችል ነው ሲሉም አንስተዋል።

የኢትዮጵያ የሚዲያ ጉዞ፣ ነጻነት፣ ኃላፊነት እና ብሄራዊ ጥቅም ላይ ያተኮረ ዘጋቢ ፊልም ቀርቧል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ያስመረቀውን የሚዲያ ልህቀት ማዕከል በተመለከተ የተለያዩ መርሃ-ግብሮችንም እያካሄደ ነው።

በዳንኤል መላኩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review