አዲስ አበባ ጎዳናዎቿን ለስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ምቹ አድርጋለች

You are currently viewing አዲስ አበባ ጎዳናዎቿን ለስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ምቹ አድርጋለች

AMN- ጥቅምት 29/2019 ዓ.ም

ከዚህ ቀደም የአዲስ አበባ ጎዳናዎች ምቹ ያልነበሩ ተሽከርካሪ እና እግረኛ እኩል የሚጋፋባቸው ለአደጋ የተጋለጡ በተለይም ታዳጊዎች አማራጭ ባለማግኘታቸው ኳስ ለመጫወት የተሽከርካሪን መንገድ የሚሻሙ ነበሩ።

ሆኖም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለስፖርት ዘርፍ በሰጠው ልዩ ትኩረት ይህ ታሪክ ሆኖ አልፏል።

ከተማ አስተዳደሩ በሚሰራቸው የልማት ስራዎች ሁሉ ለታዳጊዎች፣ ለወጣቶች እና ለሕፃናት ምቹ ከተማን በመፍጠርና ዘመናዊ መንገዶችን በመገንባት ለእግረኛ ለሳይከል እንዲሁም ለተለያዩ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ምቹ ከተማን በመገንባት ዘመን ተሻጋሪ ሥራ እየሰራ ይገኛል፡፡

በተለይም በቅርብ ጊዜ የተገነቡ እና ለህዝብ አገልግሎት ክፍት የተደረጉ አዲስ ስፖርት ፓርክ እና አራዳ ፓርክን ጨምሮ በተለያዩ ክፍለ ከተሞችና ቦታዎች የተሰሩ ዘመናዊ ሜዳዎችና የስፖርት ማዘውተሪያዎች በውስጣቸው የእግር ኳስ የቅርጫት ኳስ ሜዳ ቴንስ እና ሌሎች ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረጊያ ግብዓቶችን ያሟሉ ናቸው፡፡

አሁን ላይ የአዲስ አበባ ውብ ጎዳናዎች ሁሉን በመልኩ አድርገው በእግረኛና በሳይክል መንገድ ተውበው፣ በአረንጓዴ አበቦች አጊጠው ለእግር ጎዞ እንዲሁም ለተለያዩ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ምቹ የጤና ማዕከል መሆናቸውን የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያሳያል።

አሁን ላይ በአዲስ ጎዳናዎች ሲጓዙ በተመቻቸላቸው ጎዳናዎች እና ቦታዎች ስፖርታዊ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ወጣቶች፣ ሕፃናት፣ አረጋውያን እና ጎልማሶችን መመልከት የተለመደ ባህል ሆኗል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review