ሕገ-ወጡ የሕወሓት ቡድን በትግራይ ክልል ሕዝብ ላይ የሚፈፅመውን አፈናና ጭቆና በሚያወግዘው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የተሳተፉ ዜጎች ምን አሉ?

👉 ሕገ-ወጡ የሕወሓት ቡድን የትግራይን ሕዝብ ከልማት ወደ ኋላ ማስቀረቱን ሊያቆም ይገባል፤

👉 ሕገ-ወጡ የሕወሓት ቡድን በትግራይ ክልል ሕዝብ ላይ የሚፈጽመውን አፈናና ጭቆና ያቁም፤

👉 ለትግራይ ሕዝብ የሚበጀው የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መከበር ነው፤

👉 ሕገ-ወጡ የሕወሓት ቡድን ወጣቶችን ያለፈቃዳቸው እያፈሰ ወደ ጦር ካምፕ በማስገባት ለዳግም እልቂት እያዘጋጀ ነው፤ ይህን ድርጊቱን የሚቃወሙ እናቶችን እያሰረ ነው፤

👉 የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በተሟላ መልኩ ተግባራዊ ይሁንልን፤

👉 ሕገ-ወጡ የሕወሓት ቡድን በትግራይ ክልል እያካሄደ ያለው አፈና እና የጦርነት ዝግጅት በአስቸኳይ እንዲቆም እንፈልጋለን፤

👉 የጦርነቱ አስከፊ ጉዳት በፕሪቶሪያ ስምምነት ቢቋጭም ቡድኑ ተግባራዊ እንዳይሆን እያሰናከለው ነው፤

👉 ሕገ-ወጡ ቡድን ወጣቶችን ወደ ሱዳን የመሸጥ እና የግዳጅ አፈሳ ድርጊቱን በአስቸኳይ ማቆም አለበት፤

👉 ቡድኑ በትግራይ ክልል ወጣቶች ላይ የሚፈፅመውን አስገዳጅ ወታደራዊ ምልምላ እና እያደረሰ ያለውን ሰብዓዊ ጉስቁልና እንቃወማለን የሚሉና ሌሎች ሕገወጡ የሕወሓት ቡድን እያደረሰ ያለውን ግፍ የሚቃወሙ መልዕክቶች በሰልፉ ተሳታፊዎች ተስተጋብተዋል፡፡

በወርቅነህ አቢዮ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review