በአዲስ አበባ በአጭር ጊዜ ውስጥ እየተገነቡ ያሉ መሰረተ ልማቶች የነዋሪዎችን መሰረታዊ ፍላጎቶች የሚመልሱ ናቸው – በኢትዮጵያ የኔዘርላንድስ አምባሳደር ክሪስቲን ፒረን

You are currently viewing በአዲስ አበባ በአጭር ጊዜ ውስጥ እየተገነቡ ያሉ መሰረተ ልማቶች የነዋሪዎችን መሰረታዊ ፍላጎቶች የሚመልሱ ናቸው – በኢትዮጵያ የኔዘርላንድስ አምባሳደር ክሪስቲን ፒረን

AMN – ኀዳር 16/2019 ዓ/ም

የኢትዮጵያ እና የኔዘርላንድስ 100ኛ ዓመት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን ምክንያት በማድረግ ልዩ የብስክሌት ውድድር በአዲስ አበባ ተካሄደ።

ይህ ታላቅ የወዳጅነት መርሐ ግብር የተካሄደው በቅርቡ በተከናወነው የኮሪደር ልማት ውበት በተላበሰችው አዲስ አበባ፣ በተለይም ዘመናዊ የብስክሌት ባህል እንዲዳብርና ለነዋሪዎች ምቹ የእንቅስቃሴ ሥፍራ እንዲፈጠር ታስበው በተገነቡት ዘመናዊ የብስክሌት መንገዶች ላይ ነው።

መንገዶቹ ለከተማዋ ውበት ከመስጠት ባለፈ፣ የአረንጓዴ ትራንስፖርት አማራጮችን ለማስፋፋት እንዲሁም ዓለም አቀፍ የስፖርትና የወዳጅነት ኩነቶችን ለማስተናገድ ያላቸውን ፋይዳ በተግባር ያሳዩ ናቸው።

በኢትዮጵያ የኔዘርላንድስ አምባሳደር ክሪስቲን ፒረን እንደገለጹት፣ በአዲስ አበባ እየተገነቡ ያሉት እነዚህ መሰረተ ልማቶች የነዋሪዎችን መሰረታዊ ፍላጎቶች የሚመልሱና ተጠቃሚነታቸውን የሚያረጋግጡ መሆናቸውን ነው፡፡

የብስክሌት ጉዞ በኔዘርላንድስ ባህል ውስጥ ትልቅ ሥፍራ ያለው የዕለት ተዕለት የሕይወት ዘይቤ መሆኑ ይታወቃል ።

በመሆኑም ይህ ውድድር በአዲስ አበባ በተገነቡት አዳዲስ የብስክሌት መንገዶች ላይ መካሄዱ፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የባህል ልውውጥ ከማሳደጉም በላይ፣ ከተማዋ እየገነባች ያለችውን ጤናማና ለአካባቢ ተስማሚ የሆነ የትራንስፖርት ባህል የሚያበረታታ መሆኑን አምባሳደሯ ገልፀዋል።

በውድድሩ ላይ የሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ በኢትዮጵያ የሚገኙ የኔዘርላንድስ ዲፕሎማቶች፣ የስፖርት ቤተሰቦች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መሳተፋቸውን የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review