ዲጂታል ጥቃትን ጨምሮ ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን ለመከላከል በትኩረት እየተሰራ ነው

You are currently viewing ዲጂታል ጥቃትን ጨምሮ ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን ለመከላከል በትኩረት እየተሰራ ነው

AMN – ኅዳር 16/2019 ዓ.ም

ዲጂታል ጥቃትን ጨምሮ ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን ለመከላከል በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ሴቶች፣ ሕፃናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ገለጸ፡፡

ቢሮው በዓለም ለ35ኛ፣ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ21ኛ ጊዜ የሚከበረውን የፀረ-ፆታዊ ጥቃት ቀን አስመልክቶ ለ16 ቀናት የሚቆይ ንቅናቄ እንደሚካሄድ አስታውቋል።

ንቅናቄው «ለተጎጂዎች ፍትሕ፣ ለወንጀለኞች ተጠያቂነት፣ ለሴቶች እና ለታዳጊ ሴቶች ደኅንነት» በሚል መሪ ቃል የሚካሄድ ሲሆን፤ ፍትሕን፣ ተጠያቂነትንና ደኅንነትን ማረጋገጥ ላይ ያተኮረ ነው።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ እና የሴቶች ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ዝናሽ ከተማ፤ ፆታን መሰረት በማድረግ የሚፈጸሙ አካላዊ፣ ሥነ-ልቦናዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ዲጂታል ጥቃቶችን ለመከላከል በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ምክትል ኃላፊዋ አክለውም፣ ቢሮው ጥቃት ለደረሰባቸው ወገኖች የሕግ ከለላ እና አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

ከጥቃት ያገገሙ ሴቶች የኢኮኖሚ ጥገኛ እንዳይሆኑና ራሳቸውን እንዲችሉ ከሚመለከታቸው የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ጋር በመተባበር መልሶ የማቋቋም ሥራ እንደሚሰራም ጠቁመዋል።

በንቅናቄ ማስጀመሪያ መድረኩ ላይ የተገኙ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍል ተወካዮች በበኩላቸው፤ ፆታን መሰረት ያደረገ ጥቃት የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ርብርብ የሚጠይቅና ሁሉም ሊታገለው የሚገባ ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል።

በየምስራች ተረክበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review