የተጎሳቆሉ መንደሮች ወደ ዘመናዊና ለዜጎች ክብር የሚመጥኑ መኖሪያዎች የቀየረችው አዲስ አበባ

You are currently viewing የተጎሳቆሉ መንደሮች ወደ ዘመናዊና ለዜጎች ክብር የሚመጥኑ መኖሪያዎች የቀየረችው አዲስ አበባ

AMN – ጥቅምት 9/2019 ዓ.ም

በአዲስአበባ የተጎሳቆሉ አካባቢዎችን ወደ ንፁህ፣ አረንጓዴ፣ ለዜጎች ክብር የሚመጥን መኖሪያ ስፍራ መቀየር ተችሏል።

አብዛኞቹአካባቢዎች ለመኖር እጅግ ምቹ ያልነበሩ፤ ለሰው ልጅ ክብር የማይመጥን፤ እጅግ የቆሸሸ፣ የተፋፈገ እና የተጨናነቀ በመሆኑ የሰው ህይወትምበአስከፊ ሁኔታ በጎርፍ እና በእሳት አደጋ ያጣንበቸውን አካባቢዎች በመቀየር የነዋሪዎችን ኑሮ እና አኗኗር መቀየር እየተቻለ ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰው ተኮርነቱን በተግባር ያሳየበት እነዚህ የቤት ልማት ስራዎች እጅግ ያማሩ፥ ዘመናዊና ሁሉንም ነገር የተሟሉላቸው ናቸው።

በየአካባቢው ለነዋሪዎች የተሰሩ ቤቶች ሰፊ የስራ እድልን የፈጠሩ ፣ የንግድ ሱቆችን፣ የህጻናት የመጫወቻ ስፍራ፣የስፓርት ማዘውተሪያ( የኳስ ሜዳ፣ ቅርጫት ኳስ፣ የእጅ ኳስ፣ የመረብ ኳስ፥ የሰውነት ማጎልመሻ ቦታዎች) ፥ ለነዋሪዎች የመኪና ማቆምያ ፓርኪንግ፥ ለኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ፥ የውስጥ ለውስጥ አስፋልት መንገድ ፥ የጋራ መጠቀሚያ ሰገነት፥ ሊፍት፥ የፍሳሽና የኤሌክትሪክ መስመሮች በዘመናዊ መልክ ተሟልተው የተገነቡበት አግባብ ልዩ ያደርጋቸዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ቃሉን በተግባር እየቀየረ ትርጉም ባለው መልኩ ችግር ያለባቸውን አካባቢዎች ለሰው ልጆችየሚመጥኑ፥ ነዋሪዎች የክብርኑሮ እንዲኖሩ፥ ህይወታቸውን የሚቀይሩ ተግባራትን ያለ እረፍት 24/7 በመፈፀም ነዋሪዎች አዲስ ህይወት እንዲጀምሩ ማድረግ ላይ እየተሰራ ያለው ስራ የሚበረታታ እና ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን የአዲስ አበባ ከንቲባ ጽ/ቤት ገልጿል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review