
AMN – ታኅሣሥ 28/2017 ዓ.ም
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እድገት እና ለዴሞክራሲ መጎልበት በትጋት በመስራት፣ ለህዝባቸው እና ለሀገራቸዉ ይጠቅማል ብለው ያመኑትን በድፍረት በመታገል በሚታወቁት አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ህልፈተ ህይወት የተሰማኝን ጥልቅ ሃዘን እየገለጽኩ፣ ለቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጆቻቸው መጽናናትን እመኛለሁ ብለዋል።
ፈጣሪ ነብሳቸውን በአጸደ ገነት ያኑርልን ሲሉም አመልክተዋል።
