የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከቻይና መንግሥት የአፍሪካ ጉዳዮች ልዩ ተወካይ ጋር ተወያዩ

You are currently viewing የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከቻይና መንግሥት የአፍሪካ ጉዳዮች ልዩ ተወካይ ጋር ተወያዩ

AMN- የካቲት 7 /2017 ዓ. ም.

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከሕዝባዊት ቻይና ሪፐብሊክ መንግሥት የአፍሪካ ጉዳዮች ልዩ ተወካይ ሊ ዩሺ ጋር ተወያይተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ እና ቻይና በሁኔታዎች የማይለወጥ ሁሉን አቀፍ ስትራቴጂካዊ አጋርነት የመሠረቱ መሆኑን አስታውሰዋል።

ቻይና የኢትዮጵያ የልማት ጥረቶች ቁልፍ አጋር መሆኗንም በውይይት ወቅት መግለፃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

ሚኒስትሩ ለልዩ ተወካዩ በአፍሪካ ቀንድ እና አሕጉራዊ ሰላም እንዲሁም ጸጥታ ዙሪያ ገለጻ አድርገውላቸዋል።

ልዩ ተወካዩ ሊ ዩሺ በበኩላቸው፣ የኢትዮጵያ እና ቻይና ግንኙነት በጠንካራ መሠረት ላይ የተገነባ እንደሆነ ገልጸዋል።

በየጊዜው የሚደረጉ የከፍተኛ ባለሥልጣናት የጉብኝት ልውውጦች የሁለቱን አገራት ግንኙነት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ለመድረሱ ማሳያ ነውም ብለዋል።

ልዩ ተወካዩ በቻይና አፍሪካ መድረክ (ፎካክ) የመሪዎች ጉባኤ ላይ የተላለፉ ውሳኔዎች ኢትዮጵያ ተጠቃሚ እንድትሆን ንግድ እና ኢንቨስትመንት በማስፋፋት እና በኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታ ላይ ድጋፋችንን እናጠናክራለን ብለዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review