ባለፉት ሰባት ወራት ከሸቀጦች የወጪ ንግድ ከ3 ነጥብ 84 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ

You are currently viewing ባለፉት ሰባት ወራት ከሸቀጦች የወጪ ንግድ ከ3 ነጥብ 84 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ

AMN- የካቲት 19/2017 ዓ.ም

ባለፉት ሰባት ወራት ከሸቀጦች የወጪ ንግድ ከ3 ነጥብ 84 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዶክተር ካሣሁን ጎፌ ገለጹ።

ሚኒስትሩ በማኀበራዊ ትስስር ገፃቸው ባጋሩት መልዕክት ፤ ለገቢው መገኘት ወርቅ፣ ቡና፣ የቅባት እህሎች፣ ኤሌክትሪክ እና የቁም እንስሳት ኤክስፖርት ለውጤቱ መገኘት ከፍቸኛ አስተዋጽኦ በማበርከት የእቅዳቸውን ከ100% በላይ አፈጻጸም ማስገኘት የቻሉ የወጪ ንግድ ምርቶች መሆናቸውን ገልጸዋል።

የሰባት ወራት የወጪ ንግድ አፈጻጸም አምና በተመሳሳይ ወቅት ከተገኘው የ1.9 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ጋር ሲነፃፀር የ1.94 ቢሊዮን ዶላር ወይም የ101.2% ብልጫ እንዳለዉ መናገራቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።

አፈፃፀሙ ይበልጥ እንዲጠናከር ጥብቅ ድጋፍና ክትትል እንደሚደረጉ የተናገሩት ሚኒስትሩ የወጪ ንግድ ዘርፍ ተዋናዮችና ባለድርሻ አካላት ያለሰለሰ ጥረት እንዲያደርጉም አሳስበዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review