ዓድዋ ኢትዮጵያዊያን ከጫፍ ጫፍ በወል ተምመዉ ያስመዘገቡት ድል የጋራ ትናንትን ከነገ ጋር ያስተሳሰረ የመደመር ውጤት ነው- አቶ ሞገስ ባልቻ

You are currently viewing ዓድዋ ኢትዮጵያዊያን ከጫፍ ጫፍ በወል ተምመዉ ያስመዘገቡት ድል የጋራ ትናንትን ከነገ ጋር ያስተሳሰረ የመደመር ውጤት ነው- አቶ ሞገስ ባልቻ

AMN – የካቲት 23/2017 ዓ.ም

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ለ129ኛው የዓድዋ ድል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ኃላፊው በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፣ እኛ ኢትዮጵያዊያን በጋራ ያሳካናቸው በዓለም አደባባይ ከፍ ብለን በኩራት እንድንራመድ የሚያደርጉ ታሪካዊና ማህበራዊ መስተጋብሮች ያሉን ህዝቦች ነን ብለዋል።

የታሪካችን አሻራ፣ የብዝሃነታችን የጥንካሬያችን መሰረት መሆኑ ከተመሰከረበት አኩሪ ታሪኮቻችን አንዱ እና ዋናው የዓድዋ ድል መሆኑንም ገልጸዋል።

ዓድዋ ኢትዮጵያዊያን ከጫፍ ጫፍ በወል ተምመዉ ያስመዘገቡት ድል የጋራ ትናንትን ከነገ ጋር ያስተሳሰረ የመደመር ውጤት ነው ሲሉም አስፍረዋል።

ድሉ በመላው ኢትዮጵያዊያን የጋራ መስዋዓትነት እውን የሆነ ለሁላችን ከጀግኞች አርበኞቻችን የተበረከተ ውድ ስጦታችን ነውም ነው ያሉት ኃላፊው።

“የዓድዋ ድል ስኬታማ የሆነው በመላው ኢትዮጵያውያን የተደመረ የአንድነት መንፈስ በመሆኑ አሁንም ሆነ ወደፊት የአገራችንን እድገትና ብልጽግና የምናረጋግጠው አሰባሳቢ በሆነ ብሔራዊ ገዥ ትርክት የወል እውነቶቻችንን እያፀናን በአብሮነታችን ፀንተን ከቃል እስከ ባህል በምናደርገው በመደመር ጉዞ ነው” ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።

የአሁኑ ትውልድ በመደመር እሳቤ እስከ ቆመ ድረስ ሁለንተናዊ ብልፅግናን ማረጋገጥ እንደሚቻል አድዋ ምስክር መሆኑንም ጠቁመዋል።

በመፍጠንና መፍጠር ሁለንተናዊ ብልፅግና የተረጋገጠባት ኢትዮጵያን በጋራ እውን ልናደርግ ይገባል በማለት ኃላፊው ጥሪ አቅርበዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review