AMN ግንቦት 28/2018 ዓ.ም
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ ባሰፈሩት የኀዘን መግለጫ፣ “በቀድሞው የአዲስ አበባ ከንቲባ አምባሳደር አሊ አብዶ ህልፈተ ህይወት ጥልቅ ኀዘን ተሰምቶኛል።” ብለዋል።
አምባሳደር ዓሊ አብዶ 27ኛ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ በመሆን እንዲሁም በሱዳን እና በናይጄሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር በመሆን ሀገራቸውን ያገለገሉ የሀገር ባለውለታ መሆናቸውንም ገልጸዋል።

ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጆቻቸው እና ለመላው ሕዝብ መጽናናትን ተመኝተው፣ “ፈጣሪ ነብሳቸውን በአጸደ ገነት ያኑር” ብለዋል።