ውይይታችን በንቁ ተሳትፎ የሚገለጥ እና ጥልቀትም የነበረው ነበር።
ለጋራ እድገት እና ትብብር ያለንን ፅኑ የጋራ ተነሳሽነትም አንፀባርቀናል። የሃሳብ ልውውጣችን በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ለጠንካራ ፖለቲካዊ፣ ዲፕሎማሲያዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትስስር በር ከፍቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ፋም ሚን ቺን በቅርብ ኢትዮጵያን በሚጎበኙበት ወቅት የጋራ ርዕዮቻችንን የበለጠ የምናጠናክርበት እና በዛሬው የአለማችን አውድ የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን ይበልጥ የምናፀናበት ይሆናል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)