የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የትንሳዔ በዓልን ምክንያት በማድረግ በሁሉም ክፍለ ከተሞች እና ወረዳዎች 200 ሺህ ለሚሆኑ የኑሮ ጫና ላለባቸውና ለተለያዩ ማህበራዊ ችግር ለተጋለጡ የኅብረተሰብ ክፍሎች ማዕድ አጋርተዋል።
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕከት፣ ማዕድ ማጋራት ለነዋሪዎቻችን ፍቅራችንን እና አክብሮታችንን የምንገልፅበት እዲሁም እርስበርስ መተሳሰብን የምናዳብርበት የሰዉ ተኮር እሳቤያችን ተግባራዊ ማሳያ ነዉ ብለዋል።
እንደ ሁልጊዜው ሁሉ ዛሬም ‘መስጠት አያጎድልም’ ብለው ከጎናችን የቆሙ የከተማችን ባለሃብቶችን፣ ተቋማትን እና ወጣት በጐ ፍቃደኞችን በራሴ እና በነዋሪዎቻችን ስም ከልብ ላመሰግናቸው እወዳለሁ በማለትም ገልጸዋል።