AMN – ሐምሌ 14/2018 ዓ.ም
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በአፍሪካ ሕብረት አስቸኳይ የጤና ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ፣ የፓን-አፍሪካኒዝም ንቅናቄ መነሻዎች አንዷ በሆነችውና የታዋቂው ፓን-አፍሪካኒስት መሪ ክዋሜ ንክሩማህ ምድር ጋና አክራ መግባታቸውን ገልጸዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ፣ ትኩረቱን የአፍሪካ የጤና ስርዓትን ለማሻሻል፣ እንዲሁም ተላላፊ እና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን በመከላከል ረገድ ስልታዊ እርምጃዎችን ለመቀየስ በሚካሄደው መድረክ ላይ ምክክር እንደሚያደርጉ አመላክተዋል።

በአክራ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም በጋና ሪፐብሊክ መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና በከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል የላቀ ምስጋና አቀርበዋል።