ከንቲባ አዳነች አቤቤ የትንሳኤ በዓልን የኮሪደር ልማት ላይ ከተሰማሩ ሰራተኞች ጋር አከበሩ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ የትንሳኤ በዓልን የኮሪደር ልማት ላይ ከተሰማሩ ሰራተኞች ጋር አከበሩ

AMN – ሚያዝያ 12/2017 ዓ.ም

የትንሳኤ በዓልን የኮሪደር ልማት ላይ ከተሰማሩ ሰራተኞች ፣ኮንትራክተሮች እንዲሁም አማካሪዎች ጋር በስራ ቦታ ማክበራቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታውቀዋል፡፡

ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ ሰራተኞቹ አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ እና አዲስ ለማድረግ ቀን ከሌት ለሚያደርጉት ትጋት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የደስታ እና የመተሳሰብ እንዲሆንላቸውም ተመኝተዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review