AMN ሐምሌ 15/2018 ዓ.ም
«አዲስ አበባ» ልክ እንደ ስሟ አዲስ እና ማራኪ ሆና በድጋሚ እየተወለደች ያለችበት ምዕራፍ ላይ ናት።
በመዲናዋ እየተከናወኑ ያሉ ዘመን ተሻጋሪ የኮሪደር፥መልሶ ማልማት እና የወንዞች ዳርቻ ልማቶች የከተማዋን ገጽታ ሙሉ በሙሉ ቀይረውታል።
ከጫፍ እስከ ጫፍ የተዘረጉ ዘመናዊ መንገዶች፣ ለእግረኞች እና ለብስክሌተኞች የተሰናዱ ምቹ እና ደህንነታቸው የተጠበቁ መንገዶች፣ ለዓይን ማራኪ የሆኑ አረንጓዴ ስፍራዎች እና መናፈሻዎች ከተማዋን እጅግ ማራኪ አድርገዋታል ።

እነዚህ ሰፊ መሠረተ ልማቶች ከተማዋን ከትናንት መልኳ አላቀው ለነዋሪዎቿ የምትመችና እንዲሁም ስሉጥ የኑሮ ከባቢን ሆናለች።
የዚህ ታላቅ ለውጥ ሌላው አስደናቂ ገጽታ ፍትሃዊ የልማት ተደራሽነት መረጋገጡ ነው።
የልማት ማዕበሉ በአንድ አካባቢ ብቻ ሳይወሰን በሁሉም ክፍለ ከተሞችና ሰፈሮች ውስጥ በእኩል ደረጃ እየተዳረሰ ያለ የሀብት እና የልማት ፍትሃዊነት በግልጽ እየታየበት የሚገኝ መሆኑ ነው።
ዛሬ አዲስ አበባ የአፍሪካ የዲፕሎማሲ ማዕከልነቷን በድምቀት አስጠብቃ፣ ዓለም አቀፋዊ ደረጃዎችን የሚያሟሉ መሠረተ ልማቶችን በማሟላት የኮንፈረንስ ቱሪዝም ዋና መዲና ሆናለች።

ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የሚመጡ ታላላቅ እንግዶች የሚጎርፉባት፣ በንግድ፣ በባህልና በዕውቀት ልውውጥ ደምቃ የምትታይ፣ ቀንና ሌሊት እግር የሚበዛባት ሕያው ከተማ ሆናለች።
ይህቺን ታላቅ መዲና በሁሉ አቅጣጫ አብባና አምራ ማየት የጋራ ኩራታችን ነው።
አዲስ አበባችንን በጋራ ጠብቀንና ከፍ አድርገን ማስቀጠል የሁላችንም ታሪካዊ ሃላፊነት ነው! – የከንቲባ ጽ/ቤት