ለሕዝባችን የገባነውን ቃል በተግባር ያረጋገጥንበትን የኮሪደር ልማትና መልሶ ማልማት ሥራዎቻችንን በዛሬው ዕለት መርቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing ለሕዝባችን የገባነውን ቃል በተግባር ያረጋገጥንበትን የኮሪደር ልማትና መልሶ ማልማት ሥራዎቻችንን በዛሬው ዕለት መርቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN- ሚያዝያ 14/2017 ዓ.ም

ለሕዝባችን የገባነውን ቃል በተግባር ያረጋገጥንበት የካዛንቺስ- ሜክሲኮ- ለገሀር- ቸርችል- የእስጢፋኖስ- 4 ኪሎ ኮሪደር ልማትና መልሶ ማልማት ሥራዎቻችን በዛሬው ዕለት መርቀን ለነዋሪዎቻችን ግልጋሎት ክፍት አድርገናል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ የካዛንቺስ ኮሪደር እና መልሶ ማልማት ስራን ስንጀምር በቅድሚያ ትኩረት የሰጠነዉ እና ያሰብነው “ሰውን” ሲሆን ነዋሪዎቻችንን ፍፁም ለመኖር ምቹ ካልሆነ ሁኔታ እና አካባቢዎች በማውጣት ምቹ የመኖሪያ አካባቢን ፈጥረን ተጠቃሚ አድርገናል ነው ያሉት::

በዚህ 1 ሺህ ሄክታር መሬት በሸፈነው የካዛንቺስ የኮሪደር ልማትና መልሶ ማልማት ስራ 40.9 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ ዝርጋታ፣ 81.9 ኪሎ ሜትር የእግረኛ መንገድ ግንባታ፣ 20.7 ኪሎ ሜትር ሳይክል ሌን፣ 15 የህጻናት መጫዎቻ ቦታዎች፣ 8 የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች፣ 16 የህዝብ መዝናኛ ፕላዛዎች እና አረንጓዴ ፓርኮች፣ 19 የመጸዳጃ ቤቶች፣ 105 የንግድ ሱቆች፣ 40 የመኪና ማቆሚያዎች እና ተርሚናሎች ተካትተው መገንባቱን አመልክተዋል::

105 ሱቆችን በመገንባት ከዚህ ቀደም በአካባቢው በልማት ለተነሱ ነጋዴዎች እንዲሁም ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል ለተመረቁ ሴቶች መተላለፉንም አስታውሰዋል::

ሀገርን የመገንባት ራዕያችን እውን እንዲሆን ለልማት የተነሳችሁ ነዋሪዎቻችን፣ በገንዘብ፣ በጉልበት እንዲሁም ሃብት በማስተባበር ሃገር በጋራ ለማነፅ በቅንነት ከጎናችን ለቆማችሁ ባለሃብቶች፣ ኮንትራክተሮች፣ አማካሪዎች እንዲሁም አመራሮች ሁሉ በከተማ አስተዳደራችን ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ ሲሉም ገልጸዋል::

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ላደረጉት ድጋፍ እና ክትትልም በራቸው እና በነዋሪዎች ስም ምስጋና አቅርበዋል::

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review