በታሪካዊው የሀገራዊ ምክክራችን ዋዜማ፣ የኢትዮጵያ ታላቅ ወዳጅ የሆኑትን ኦሊሴጉን ኦባሳንጆን በጽሕፈት ቤቴ ተቀብያለሁ- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

AMN – ሐምሌ 07/2018 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት ዛሬ በታሪካዊው የሀገራዊ ምክክራችን ዋዜማ፣ የኢትዮጵያ ታላቅ ወዳጅ የሆኑትን ኦሊሴጉን ኦባሳንጆን በጽሕፈት ቤቴ ተቀብያለሁ ብለዋል፡፡

በመጪው ሀገራዊ ምክክር ዙሪያ ለመወያየት እንዲሁም ከዚህ ቀደም ካከናወኗቸው ተግባራት ጥበብ ለመቅሰም ችለናል፤ በተለይም የቢያፍራን የሰላም ሂደት በመምራት ያካበቱትን ልምድ አጋርተውናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገልጸዋል።

ይህም ኢትዮጵያ በምክክር ለምታረጋግጠው አንድነትና ዘላቂ የሰላም ጉዞ ላይ ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ ነው በማለት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባጋሩት መልዕክት አንስተዋል።

ኢትዮጵያ ለምታበረክቱት በዋጋ የማይተመን አስተዋጽኦ ሁልጊዜም የላቀ ምስጋናዋን ታቀርባለች ሲሉም አክለዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review