በመዲናዋ ባለፉት 11 ወራት ብቻ ከ56 ሺህ በላይ እግረኞች መቀጣታቸውን ትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን አስታወቀ

You are currently viewing በመዲናዋ ባለፉት 11 ወራት ብቻ ከ56 ሺህ በላይ እግረኞች መቀጣታቸውን ትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን አስታወቀ

AMN- ሰኔ 9/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 11 ወራት ብቻ 56 ሺህ 332 ተገቢውን የመንገድ አጠቃቀም ስርዓት ያልተከተሉ እግረኞች መቀጣታቸውን ትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን አስታውቋል፡፡

በከተማዋ ተገቢውን የመንገድ አጠቃቀም ስርዓት ያልተከተሉ እግረኞች ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን በአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት የትራፊክ ቁጥጥርና ኩነት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አያሌው አቲሳ ለአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ኤፍ ኤም 96.3 ገልጸዋል፡፡

ባለፉት 11 ወራት በተካሄደ ቁጥጥርም የእግረኛ ማቋረጫ /ዜብራ/ ላይ ያልተሻገሩ፣ በተሽከርካሪ መንገድ ላይ የተጓዙ፣ ተሽከርካሪን ከፊት እያዩ ያልተጓዙ እና ሌሎችም ጥፋት የተገኘባቸው 29 ሺህ 489 እግረኞች በገንዘብ የተቀጡ ሲሆን፣ 26 ሺህ 843 እግረኞች ደግሞ በማህበራዊ አገልግሎት በአጠቃላይ 56 ሺህ 332 እግረኞች መቀጣታቸውን ተናግረዋል፡፡

ለከተማዋ ትራፊክ ፍሰት መሳለጥ የእግረኞች የመንገድ አጠቃቀም እንቅፋት ሲፈጥር እንደነበር ያስታወሱት አቶ አያሌው አቲሳ፣ አሁን ላይ በከተማዋ የኮሪደር ልማት ለእግረኞች ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን ጠቁመዋል፡፡

በከተማዋ ስርዓት ያለው የመንገድ አጠቃቀም እውን እንዲሆን በግንዛቤ የተደገፈ የእግረኛ ቁጥጥር ሥራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ኃላፊው ጠቁመዋል፡፡

በሂሩት ብርሃኑ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review