የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ያለፉት ዓመታት ውጤትና እውነታዎች

You are currently viewing የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ያለፉት ዓመታት ውጤትና እውነታዎች

AMN- ሰኔ 20/2017 ዓ.ም

-ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት ስድስት ዓመታት በተከናወነው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ወደ 40 ቢሊየን የሚጠጉ ችግኞች የተተከሉ ሲሆን፣ በዚህም ተመናምኖ የነበረውን የደን ሽፋን ደረጃ ከ17.2 ወደ 23.6 በመቶ ማሳደግ ተችሏል፤

-ባለፉት ስድስት ዓመታት ከተተከሉ ከ40 ቢሊየን ችግኞች መካከል 60 በመቶ የሚሆነው ለምግብነት የሚውሉ የፍራፍሬ ችግኞችና ለእንስሳት መኖ የሚሆኑ በጥምር ደን እና በእርሻ ማሳዎች የተተከሉ ናቸው፤

-አረንጓዴ አሻራው በምግብ ራስን በመቻል ገበያ ተኮር የሆኑ አቮካዶ እና መሰል ፍራፍሬ ምርቶች ማህበረሰቡ አንዲያመርት እና ለገበያ እንዲያቀርብ በማስቻል ውጤት ተገኝቷል፤

-የአካባቢ ጥበቃ ሥራ ትኩረት እንዲያገኝ በመደረጉ እየተመናመኑ ያሉ የሀገር በቀል ችግኞችን ዳግም በመትከል የተራቆተ መሬት ምጣኔም ከ6 ሚሊየን ሄክታር ወደ 2.5 ሚሊየን ሄክታር ማውረድ ተችሏል፤

-የጎርፍ አደጋዎች እንዲሁም ድርቅና የመሬት መንሸራተት ችግሮች በከፊል እንዲቀንሱ የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም የሚችል ኢኮኖሚ ጭምር ለመፍጠር ትርጉም ያለው ውጤት ተገኝቷል፤

-እንደ አዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ዓመታት በዚህ መርሐ-ግብር በተሰሩ ስራዎች፣ በከተማዋ በስፋት እየተከናወኑ ካሉት የኮሪደር ልማት እና የወንዝ ዳርቻዎች ልማት ጋር የተሳሰረ እንዲሆን በማድረግ ውጤታማ ስራዎች ተሰርተዋል

-የአረንጓዴ አሻራ ስራዎች እንደ ሀገር የአረንጓዴ ባህልን ለመፍጠር፣ የአየር ንብረት ለዉጥን ለመከላከል፣ የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ የስራ ዕድልን በመፍጠር እና የአየር ንብረት ዲፕሎማሲን በማጠናከር ረደግ ትልቅ ሚና አለው፤

-የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር በስፋት በመከናወኑ ኢትዮጵያ ያላትን የብዝሀ ህይወት ሀብት እና ፀጋ በአግባቡ እንድትንከባከብ ዕድል የሰጠ እንደሆነ የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review