በዘንድሮው የበጀት ዓመት 233 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ መቻሉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ

You are currently viewing በዘንድሮው የበጀት ዓመት 233 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ መቻሉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ

AMN ሃምሌ 02/2017

በዘንድሮው በጀት ዓመት 241.4 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 233 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ የዕቅዱን 96.5 % ማሳካት መቻሉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ይህም ከባለፈው በጀት ዓመት 83.3 ቢሊዮን ብር ብልጫ ያለው ወይም 45 በመቶ እድገት በከተማዋ ገቢ ላይ እድገት ያሳየ ነው። ያልተሰበሰበው 8 ቢሊዮን ብር ከእርዳታ እና ብድር ይገኛል ተብሎ በተጨማሪ በጀት የታወጀ ነበር።

ለውጥና እድገት በራስ አቅም ሲሆን መሰረቱ ሰፊ፤ ምሰሶውም ጠንካራ ይሆናል።

ውድ የከተማችን ነዋሪዎች፤ ውድ ግብር ከፋዮቻችን፤ ውድ የገቢዎች ቢሮ ሰራተኞችና አመራሮች እንዲሁም ወድ ባለድርሻ አካላት ለተገፕዉ ስኬት በራሴ እና በከተማው አስተዳደር ስም እዲሁም በከተማችን ነዋሪዎች ስም አመሰግናለሁ።

ነገም አቅማችን እናተዉ ናችሁና ፤ ችግሮችን እያረምን በራስ አቅም፣ በትብብር፣ በጠንካራ እምነት እና የስራ ባህል የመራናት ከተማችን እድገት ይቀጥላል ብለዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review