በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ በጉጉት የተጠበቀው የባርሰሎና እና ፓሪሰን ዠርማ ጨዋታ በፈረንሳዩ ክለብ 2ለ1 አሸናፊነት ተጠናቋል።
በኢስታዲዮ ኦሎምፒኮ ሊውስ ካምፓኒ በተደረገው ጨዋታ ባርሳ ፌራን ቶሬስ ባስቆጠረው ግብ መምራት ቢችልም ውጤቱን አላስጠበቀም። ፒ ኤስ ጂ ሴኒ ማዩሉ እና ጎንካሎ ራሞስ ግቦች ሦስት ነጥቡን ወስዷል።
በሊውስ ኤነሪኬ የሚመራው ቡድን ባሎን ድ ኦር አሸናፊው ኡስማን ዴምቤሌን ጨምሮ ስድስት ወሳኝ ተጫዋቾቹን በጉዳት ምክንያት አልተጠቀመም።

በሌሎች ጨዋታዎች አርሰናል በጋብርኤል ማርቲኔሊ እና ቡካዮ ሳካ ግቦች ኦሎምፒያኮስን 2ለ0 ማሸነፍ ሲችል ፤ ማንችስተር ሲቲ ከሞናኮ 2ለ2 ተለያይቷል። ለሲቲ ኧርሊንግ ሃላንድ ሁለቱንም ግቦች ከመረብ አሳርፏል። ናፖሊ በራስመስ ሆይሉንድ ሁለት ግቦች ታግዞ ስፖርቲንግ ሊዝበንን 2ለ1 አሸንፏል።
ቦሩሲያ ዶርትመንድ አትሌቲክ ቢልባኦን 4ለ1 ሲረታ ቪያሪያል ከ ጁቬንቱስ ጨዋታቸውን 2ለ2 አጠናቀዋል። ባየር ሊቨርኩሰን ከ ፒ ኤስ ቪ አይንዶቨን ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ መጠናቀቅ ችሏል።
በሸዋንግዛው ግርማ