በ2010 ዓመተ ምህረት በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተጀመረው ይኽ ሥነሥርዓት የዜግነት የግብር ግዴታቸውን በወቅቱ እና በታማኝነት የሚፈፅሙ ዜጎችን ለማበረታታት ታቅዶ የሚተገበር ነው።

በዘንድሮው መርሃ ግብር 700 ታማኝ ግብር ከፋዮች እውቅና ተሰጥቷቸዋል። በ2017 ዓመተ ምህረት እንደነበራቸው አስተዋጽኦ መጠን 105 የፕላቲኒየም ደረጃ፣ 245 የወርቅ ደረጃ፣ 350 ደግሞ የብር ደረጃ ተሸላሚ ሆነዋል። የጋራ አስተዋጽኦዋቸው በሥራ ዘመኑ 900.22 ቢሊዮን ብር በግብር እንዲሰበሰብ አስችሏል።

በተጨማሪም የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን በግብር እና ቀረጥ አሰባሰብን ብቁ እና ግልፅ የሚያደርጉ የዲጂታል ሥርዓቶችን አስጀምረዋል። ከነዚህም ውስጥ የኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ ሥርዓት፣ ኤሌክትሮኒክ የጉምሩክ አስተዳደር ሥርዓት እና ኤሌክትሮኒክ የጭነት መከታተያ ሥርዓት ይገኙበታል – የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት