ደራሲ፣ የሃይማኖት ምሁር እና የሥነ ፈለክ ባለሙያ መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶ/ር) የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል፡፡
መላው የሰው ዘር ዓድዋን ሲያስብ ነጻነትን እና ድልን ያስባል ያሉት መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶ/ር) በዓድዋ ድል መታሰቢያ በነበራቸው ቆይታ እንደተደሰቱ ገልፀዋል፡፡
የዓድዋ አርበኞች ነጻነታችንን ለማስጠበቅ ደማቸውን አፍሰዋል፤ አጥንታቸውን ከስክሰዋል፤ ለነሱ መታሰቢያ እንዲሆን የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዚህ መልኩ መገንባቱ አስደስቶኛል ሲሉ ሃሳባቸውን አካፍለዋል፡፡
የሥነ ፈለክ ባለሙያው መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ፤ በነበራቸው ጉብኝት ዛሬ ላይ ሆኜ ትላንትን ማየት ችያለሁ ያሉ ሲሆን ዓድዋ በአፍሪካዊያን ልብ ውስጥ ታትሞ የሚቀመጥ ነው ሲሉ ገልጸውታል፡፡
ስር የሌለው ግንድ፤ ግንድ ያልተሸከመው ቅርንጫፍ የለም፤ ስሮቻችን ቅድመ አያቶቻችን ናቸው፤ ግንዱ እኛ ነን፤ ቅርንጫፎቻችን ከኛ የሚገኙ የልጅ ልጆች ናቸው፤ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ዛሬ ላይ ቆሜ ወደ ኋላ እንዳስብ አድርጎኛል ማለታዉቸዉን የዓድዋ ድል መታሰቢያ ለኤኤምኤን ዲጂታል ሚዲያ በላከዉ መረጃ አስታዉቋል፡፡