በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የተሰሩ የልማት ስራዎች በመንግስት የሚገቡ ቃሎችን በተግባር ያረጋገጡ መሆናቸዉን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ደኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ ገለፁ፡፡
ሚኒስትር ዴኤታዉ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የተገነቡ እና እየተገነቡ ያሉ የልማት እንቅስቃሴዎችን ተመልክተዋል፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ ላይ የተሰራዉ የኮሪደር ልማትን የጎበኙት አቶ ተስፋሁን ፣ በአዲስ አበባ ከተማ የተሰራው የልማት ስራዎች ከተማን የመገንባት ብቃት ያረጋገጡ ስለመሆናቸው አስረድተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ የኮራደር ልማት ተሞክሮ በክልል ከተሞች ላይም እዉን በማድረግ ከተሜነትን ለማስፋት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ፕሮጀክቶችን መጀመር በተያዘላቸዉ ጊዜ ይጠናቀቁ ዘንድ ሁለንተናዊ ርብርብን በማድረግ ለህዝብ ግልጋሎት ክፍት ማድረግ የመንግስት መለያ መሆኑን አመላክተዋል።
ሚኒስትር ደኤታዉ በማዕከላዊ ኢትዮጵያም ይህ የመንግስት ልዩ መገለጫ በዉል እየታየ ነዉ ብለዋል፡፡
በቀጣይም ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሀገርንወደ ተሻለ እድገት የሚያስፈነጥሩ ልማቶች በመላ ሀገሪቱ ተግባራዊ እየተደረ ይገኛል ብለዋል።
ከዚህ በተጨማሪ መገናኛ ብዙሀን የልማት አቅሞችን እና የህዝብ አብሮነት እና ተጠቃሚነትን ማሳየት እና ማስገንዘብ ላይ ሊሰሩ እንደማገባም ሚኒስትር ዴኤታዉ አንስተዋል፡፡
በተመስገን ይመር