ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከጎሮ መታጠፊያ እስከ ኮዬ ፈጬ አደባባይ ድረስ ያለውን አዲስ የኮሪደር ልማት ስራን አስጀመሩ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከጎሮ መታጠፊያ እስከ ኮዬ ፈጬ አደባባይ ድረስ ያለውን አዲስ የኮሪደር ልማት ስራን አስጀመሩ

AMN ሰኔ 11/2018 ዓ.ም

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት ከጎሮ መታጠፊያ እስከ ኮዬ ፈጬ አደባባይ ድረስ ያለውን አዲስ የኮሪደር ልማት ስራን በተቀናጀና በተደራጀ አግባብ ጀምረናል ብለዋል፡፡

ከጎሮ መታጠፊያ – ኮዬ ፈጬ አደባባይ ያስጀመርነው የኮሪደር ልማት አጠቃላይ የመንገዱ ርዝመት 10.5 ኪሎ ሜትር ሲሆን፣ የመንገዱ ስፋት 70 ሜትር (ስምንት ሌን ያለው) ከነግሪነሪው 124 ሜትር፣ 21 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የሳይክል መንገድ፣ 21 ኪሎ ሜትር ርዝመት እና በሁለቱም በኩል 4.5 ሜትር ስፋት ያለው የእግረኛ መንገድ፣ ሰፊ የአረንጓዴ ሽፋን እንዲሁም የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያም ይኖረዋል ብለዋል፡፡

ኮሪደር ልማቱ በከተማችን ቀደም ሲል የለሙ መሰረተ ልማቶችን በከፍተኛ ሁኔታ የሚያስተሳስር፣ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴውን የሚያነቃቃ ፣ በመንገዱ ላይ ያለውን የትራፊክ መጨናነቅ የሚፈታ፣ ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ጋር የተገናኘ በመሆኑም ሀገራዊ ሁነቶችን ለማስተናገድ አመቺ ሁኔታን የሚፈጥር፣ እንዲሁም የአካባቢውን ስታንዳርድ በእጅጉ በሚያሳድግ ሁኔታ የሚሰራ ነው ።

በተጨማሪም በኮሪደሩ ሞሎች፣ የቢዝነስ ተቋማት እና ሌሎች ኮሚኒቲዎች የሚገነቡ ሲሆን ከዚህ ቀደም በመንገዱ ዙሪያ ከደረጃ በታች ይሰጡ የነበሩ አገልግሎቶችን ከፍ ባለ ደረጃ ለመስጠት በሚያስችል መልኩ በጥራትና በፍጥነት ለማጠናቀቅ በትልቅ ርብርብ የምንሰራው ይሆናል ብለዋል፡፡

ይህ ኮሪደር ከከተማችን እልፎ ሀገራዊ ፋይዳ ያለው፣ ለአካባቢው ነዋሪ ሰፊ የስራ እድል የሚፈጥር፣ አካባቢውን ወደ ትልቅ የንግድ እንቅስቃሴ የሚቀይር በመሆኑ በአካባቢው ላይ የምትኖሩ የከተማችን ነዋሪዎች ትብብራችሁ እንደ ወትሮው የተጠናከረ እንዲሆንና አብረን እንድንሰራ፤ እንዲሁም በስራው ውስጥ የምትሳተፉ ኮንትራክተሮች፣ ማህበራት፣ አማካሪዎች በአጠቃላይ ባለድርሻ አካላት በትብብር በፍጥነት በጋራ እንድናሳካው ጥሪዬን አቀርባለሁ ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

Se

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review