መንግስት ለሰው ተኮር አጀንዳዎች ልዩ ትኩረት በመስጠት ለአካታች ልማት እየሰራ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ

You are currently viewing መንግስት ለሰው ተኮር አጀንዳዎች ልዩ ትኩረት በመስጠት ለአካታች ልማት እየሰራ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ

AMN ኅዳር 9/2018 ዓ.ም

መንግስት ለሰው ተኮር አጀንዳዎች ልዩ ትኩረት በመስጠት ለአካታች ልማት እየሰራ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገልጸዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት በደሴ ከተማ የተመለከትናቸው የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርት ግብይት ማዕከል እንዲሁም የእንጀራ መጋገራሪያ አዳራሽ ስራዎች የሕዝባችንን የየዕለት ችግሮች ለመፍታት ለምናደርገው ጥረት ማሳያዎች ናቸው ብለዋል፡፡

የግብይት ማዕከሉ ዋና ዓላማ አምራቾች እና ሸማቾችን በማገናኘት እና በመካከል ያለውን የተንዛዛ የግብይት ሰንሰለት በማሳጠር ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ገበያን ማረጋጋት ነው።

ማዕከሉ የግብርና፣ የኢንዱስትሪ፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን እና የእንስሳት ተዋጽኦዎች ግብይት ይካሄድባቸዋል ብለዋል፡፡

የደሴ ከተማ የቧንቧ ውሃ የእንጀራ መጋገራሪያ አዳራሽ ግንባታ እንጀራ በመጋገር ዘላቂ የሥራ ዕድል በመፍጠርና ምርታማነትን በማስፋፋት የዜጎች ተጠቃሚነትን ማረጋገጥን ዓላማ ያደረገ ነው።

የብልጽግና ጉዟችን ሁሉንም ማኅበረሰብ ተጠቃሚ በማድረግ ማኅበራዊ ፍትህን ያረጋገጠ ዘላቂ ልማትን በማረጋገጥ ራዕይ የሚመራ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review