ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋን በቢሮአቸው ተቀብለው አነጋገሩ

You are currently viewing ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋን በቢሮአቸው ተቀብለው አነጋገሩ

AMN ኅዳር 24 ቀን 2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋን በቢሮአቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

‎ኮሚሽነር ጀነራል የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ የፖሊስ ለፖሊስ ግንኙነትን የበለጠ በማጠናከር ሽብርተኝነትንና ሌሎች ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በጋራ ለመከላከል፣ በልምድ ልውውጥ፣ በአቅም ግንባታ በትብብር አብሮ ለመስራት ከአምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ጋር ሰፊ ውይይት አድርገዋል።

‎አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ በበኩላቸው የሁለቱን ሀገራት ፖሊስ ለፖሊስ ግንኙትን የበለጠ ለማሳደግ ሀገራቸው ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት ገልፀው በተለይም ሽብርተኝነትና ሌሎች ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በጋራ እና በትብብር ለመከላከል አሜሪካ ቁርጠኛ መሆኗን በውውይቱ ወቅት ማረጋገጣቸዉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ለኤኤምኤን የላከዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review