የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አገልግሎቶቱን በኦን ላይን መስጠት መጀመሩን አስታወቀ

You are currently viewing የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አገልግሎቶቱን በኦን ላይን መስጠት መጀመሩን አስታወቀ

AMN ታህሳስ 03/ 2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከዚህ ቀደም የሙከራ ምዕራፍ ላይ የነበረውን አገልግሎት በኦላይን መስጠት የሚያስችል ቴክኖሎጂን ወደ ሙሉ ትግበራ ምዕራፍ ማስገባቱን ይፋ አድርጓል ።

በስነ ስርዓቱ ላይ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አይሻ ሞሐመድ ተቋሙ ቀደም ሲል በአዲስ መሶብ ውስጥ በተካተቱት እና አገልግሎትን በኦላይን መስጠት ከጀመሩ መስሪያቤቶች መካከል አንዱ መሆኑን ጠቁመዋል።

በሙከራ ላይ የነበረው እና አሁን ሙሉ ለሙሉ ወደ ትግበራ የገባው አሰራርም ደንበኞች ቢሮ መምጣት ሳይጠበቅባቸው ባሉበት ስፍራ ሆነው ኮሚሽኑ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ማግኘት የሚያስችላቸው እንደሆነ ዋና ኮሚሽነሯ ተናግረዋል።

ባለሃብቱ ባለበት ሆኖ የኢንቨስትመንት አገልግሎቶችን (Online Service) እንዲያገኝ የሚያስችል ጥራትና ቅልጥፍናን ያስተሳሰረ አገልግሎት ለመስጠት እና ከቅንጅታዊ መስሪያ ቤቶች ጋር ያለምልልስ በኦን ላይን ስራዎችን ለመጨረስ የሚያስችል መሆኑን ገልፀዋል።

የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ግርማ ቤካ በበኩላቸው ደንበኞች ቴክኖሎጂውን በአግባቡ እንዲጠቀሙ የሚያስችል አጋዥ ባለሙያዎችን መመደባቸውን ገልፀው ሲስተሙ ከፋይዳ ጋር የተሳሰረ በመሆኑ ትውልደ ኢትዮጵያን ጭምር ባሉበት ሆነው እንዲስተናገዱ የሚያስችል ነው ብለዋል።

ለአገልግሎት የሚያስፈልጉ ክፍያዎችም ለመፈፀም ከቴሌ ብር እና ከንግድ ባንክ ጋር እንዲተሳሰር መደረጉንም ምክትል ኮሙሽነሩ አብራርተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አዋሌ ሞሐመድ እንደከተማ በዲጅታላይዜሽን ዘርፍ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙ ገልፀው የድህረገፆችን ደህንነት አስተማማኝ ለማድረግ ሰፊ ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

በታምሩ ደምሴ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review