ኢትዮጵያና ሕንድ ከ2ሺህ አመታት በላይ የቆየ ታሪካዊ ግንኙነት እንዳላቸዉ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
ሁለቱ ሀገራት ዘመናዊ የሚባለዉን ዲፕሎማሲ የጀመሩት በ1948 ዓ.ም ሲሆን በ1952 ዓ.ም ሲሆን ዲፕሎማሲው በአምባሳደር ደረጃ ከፍ ብሏል።
ከአፍሪካ ሀገራት በኒው ዴልሂ ኤምባሲዋን የከፈተችዉ የመጀመሪያዋ ሀገርም ኢትዮጵያ ሆናለች፡፡
ለዘመናት የቆየዉ የሁለቱ ሀገራት ትብብር በኢኮኖሚዉ ዘርፍም ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ የብሪክስ አባል ሀገራት ሆነዉ በጋራ በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙት የውጭ ሀገራት ባለሀብቶች መካከል ሕንድ ከቀዳሚዎቹ ሦስት ሃገራት አንዷ ስትሆን፣ ከ4 ቢሊዮን ዶላር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ከ500 በላይ የሕንድ ኩባንያዎች በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች ላይ ተሰማርተዉ በመሥራት ላይ ይገኛሉ፡፡
ሕንድ የኢትዮጵያ ሁለተኛዋ ትልቅ የንግድ አጋር ስትሆን ከፍተኛ የንግድ ልውዉጥ በማድረግም ይታወቃሉ፡፡
ሁለቱ ሀገራት በግብርና፣ በጤና፣ በመከላከያ፣ በታዳሽ ኃይልና በሌሎች ዘርፎች ጠንካራ ትብብር ያላቸዉ ሲሆኑ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ደግሞ በማዕድን ልማት፣ በዲጂታል፣ በሕዝብ መሠረተ ልማትና በሳይበር ደኅንነት መስኮች አዲስ ግንኙነት ማድረጋቸዉን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
በወንድማገኝ አሰፋ